በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ሴቶች ወደፊት እንዲመጡ ማብቃት እና ማገዝ ያስፈልጋል

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ላይ ሴቶች ወደፊት እንዲመጡና የመሪነት ሚናን መጫወት እንዲችሉ ማብቃት እና ማገዝ እንደሚያስፈልግ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ገለጹ።

በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ዱባይ እየተካሄደ በሚገኘው የጂ.አይ.ቴክስ ኤክስፖ (GITEX 2024) ሴቶች በሳይበር ደህንነት ላይ ባላቸው ተሳትፎና መጫወት በሚችሉት ሚና ዙሪያ የፓናል ውይይት ተካሂዷል። በውይይቱ ላይ በፓናሊስትነት የቀረቡት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ሴቶች ወደፊት መምጣት እንዲችሉ፤ በአንድ በኩል ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ማድረግ የሚያስፈልግ ሲሆን በሌላም በኩል ሴቶች እራሳቸውን ማብቃትና ተወዳዳሪ ሆነው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

ኢትዮጵያ በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ሴቶች ወደፊት እንዲመጡ የሚያስችሉ እርምጃዎችን፤ በፓሊሲና በተለያዩ የሕግ ማዕቀፎች የመደገፍ፣ በተለያዩ የቴክኖሎጂና የሳይበር ደህንነት ኢኒሼቲቮች ላይ እንዲሳተፉ በማበረታታት ወ.ዘ.ተ እየሰራች ያለችውን ሥራ አብራርተዋል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የተቋሙ ሴት አባላት ወደ አመራርነት እንዲመጡም ይሁን በአጠቃላይ በሁሉም መስክ ውጤታማ እንዲሆኑ ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነም ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ በመድረኩ ለይ አብራርተዋል።

Publicador de Conteúdos e Mídias


የቅርብ ዜናዎች