የመከላከያ ሰራዊቱን ጀግንነት የዘመናችን የውጊያ ምህዳር በሆነው በሳይበር ምህዳር መድገም እንደሚገባ ተገለጸ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የመከላከያ ሰራዊታችን ጀግንነት የዘመናችን የውጊያ ሜዳ በሆነው “የሳይበር ምሕዳር” ላይም መድገም እንደሚገባ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ትግስት ሃሚድ ገለጹ፡፡

ይህ የተገለጸው በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አማካኝነት ለሦስት ወራት ያህል የሳይበር ደህንነት የአቅም ግንባታ ስልጠና ሲሰለጥኑ የቆዩ የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት አባላት በዛሬው ዕለት በተመረቁበት ወቅት ነው፡፡

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ክብርት ወይዘሮ ትግስት ሃሚድ የሳይበር ምህዳር የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ፣ የባህል፣ የዲፕሎማሲ እና የወታደራዊ እውቀትና ፍልስፍናዎች የሚራመዱበት፣ የሚተሳሰሩበትና ለሁሉም ተዋናዮች እኩል እድልና አቅም ያስገኘ ምህዳር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

“ይህን በዉል የተገነዘቡ ሀገራት በመስኩ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋያቸዉን በማፍሰስና የሳይበር ጦራቸዉን መገንባት ችለዋል። በዚህ ሂደትም የመረጃ የበላይነትን በማረጋገጥ ጦርነትን በበላይነት ማጠናቀቅ የሚያስችል አቅም ፈጥረዋል” ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ፤ ይሁን እንጅ ምህዳሩን በአግባቡ አውቀው ካልተጠቀሙበትና በተከታይነት ሳይሆን በመሪነት ካልተሳተፉበት ለበርካታ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ እንዲሁም የደህንነት ችግሮች የሚያጋልጥ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በዚህ ረገድ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር “የኢንፎርሜሽን የበላይነትን ማረጋገጥ የሚችል ብሔራዊ አቅም እውን ሆኖ ማየት” ራዕይዉ አድርጎ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን ባለፉት 17 ዓመታትም በሰዉ ኃይል ልማት፣ በቴክኖሎጂ ባለቤትነት በማረጋገጥ እንዲሁም የአሰራር ስርዓቶችን በመዘርጋት ሰፊ አቅሞችን መፍጠር ችሏል።

የመከላከያ ሰራዊታችንም የሀገራችንን ዳር ድንበር እና ሉዓላዊነት በደምና በአጥንቱ ያስከበረ ፍጹም ኢትዮጵያዊ እና ጀግና ሰራዊት እንደሆነ እኛ ብቻ ሳንሆን ሌሎች ሀገራትም ጭምር የሚመሰክሩለት መሆኑን ያመላከቱት ዋና ዳይሬክተሯ፤ “ይህ የመከላከያ ሰራዊታችን ጀግንነት የዘመናችን የውጊያ ወይም የጦርነት ምህዳር በሆነው “የሳይበር ምሕዳር” ላይም መድገም ይገባል” ብለዋል፡፡ ለዚህም ምህዳሩን የሚመጥን እውቀት፣ ክህሎት እና አስተሳሰብ መላበስና በቀጣይነት እያሳደጉ መሄድ ግድ ይላል፡፡

በመሆኑም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የተወለደ ተቋም እንደመሆኑ መጠን የሰራዊቱን ሁለንተናዊ አቅም ለማጎልበት ሁሌም ዝግጁ መሆኑን ያስታወሱት ዋና ዳሬክተሯ፤ በዚህም ባለፉት ጊዜያት በተለያዩ መስኮች በጋራ ሲሰራ መቆየቱንና ወደፊትም በጋራና በቅንጅት የሚሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ተመራቂዎቹ በስልጠናው ያገኙትን ዕውቀትና ክህሎት የሀገራችን ብሄራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ፣ የዲጂታል ሉዓላዊነታችንን ለማረጋገጥ እንዲሁም የብሄራዊ ደህንነት ስጋትን ለመቀነስ መሳሪያ አድርገው እንደሚጠቀሙበት ያላቸውን ዕምነት የገለጹት ዋና ዳይሬክተሯ፤ ነገር ግን ዘርፉ ተለዋዋጭና አዳጊ በመሆኑ ተመራቂዎቹ የሰራዊቱ አባላት ከዘርፉ ጋር አብሮ የሚሄድ ቀጣይነት ያለዉ የመማርና የማደግ ጉዟቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉበት አደራ ብለዋል፡፡

Publicador de Conteúdos e Mídias


የቅርብ ዜናዎች