ማስጠንቀቂያ (Caution)

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የፊሺንግ የሳይበር ጥቃት (Phishing Cyber Attack) እየተበራከተ መጥቷል፡፡ ይህ የሳይበር ጥቃት በኢ-ሜይል፣ በቴሌግራም፣ በፌስቡክ እና በሌሎች ማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የሚላኩ ሀሰተኛ ግን ተመሳስለው የተሰሩ ሊንኮች (Links) ናቸው፡፡ የሚላኩት ሊንኮች ሰዎች በሚወዱት፣ በሚፈልጉት (ስኮላርሺፕ፣ የሎተሪ አሸናፊ ነዎት በሚል ወ.ዘ.ተ)፣ በሚያስደነግጣቸው ወይም ሌላ ፈጣን ምላሽ እንዲሰጡ ከሚያደርግ አጭር የጽሁፍ መግለጫ ጋር ይላካል፤ ሊንኩን ጠቅ ባደረግንበት ቅጽበት (በምንከፍትበት ወቅት) የማህበራዊ ገጻችንን የይለፍ ቃል፣ የተጠቃሚ ስም/ ባለቤትነትን/ እና ሌሎች ግላዊ መረጃዎችን ይመነትፋሉ ወይም ወደሌላ ገጽ በመውሰድ የሚፈልጉትን መረጃ ፎርም እንድንሞላ ያደርጉናል፡፡

ጥቃቶቹ በአብዛኛው በርካታ ተከታይ ያላቸውን ተቋማት ወይም ግለሰቦች የማህበራዊ ሚዲያ ገጽ ዒላማ የሚያደርግ ነው፡፡

መወሰድ ያለበት የጥንቃቄ እርምጃ

• የተላኩትን ሊንኮች ከመክፈታችን በፊት የላከውን አካል ማንነት ማጣራት፤

• የተላከው ሊንክ ከምናውቃቸው ሊንኮች ጋር አንድ መሆን አለመሆኑን ማረጋገጥ፤

• ከተጠራጠርን ፈጽሞ ሊንኮቹን አለመክፈት፤

• የማህበራዊ ገጻችን ቢጠለፍ እና ከእኛ ቁጥጥር ውጪ ቢሆን ያን ገጽ ላቀረበው አካል በሌሎች አካውንትም ቢሆን ገብተን መጠለፉን በማሳወቅ እንዲመለስ ማድረግ እንችላለን፡፡

በተጨማሪም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ነጻ የስልክ መስመር 933 በመጠቀም ጥቆማ እና ምክር ማግኘት ይችላሉ፡፡

Publicador de Conteúdos e Mídias


የቅርብ ዜናዎች