ቋሚ ኮሚቴው የኢንፎርሜሽን መረብ ደሕንነት አስተዳደርን የሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ገመገመ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢንፎርሜሽን መረብ ደሕንነት አስተዳደርን የሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ገምግሟል፡፡

አስተዳደሩ በሩብ ዓመቱ ያከናዎናቸውን ተግባራት እና ያጋጠሙት ችግሮችን በተመለከተ ቋሚ ኮሚቴው በስፋት ተወያይቶባቸዋል፡፡

የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ዲማ ኖጎ (ዶ/ር) አስተዳደሩ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አስገንዝበው፣ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ከአስተዳደሩ ጋር በጋራ እንደሚሰሩ ጠቅሰዋል ፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደሕንነት አስተዳደር ዋና ዳሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ በበኩላቸው አስተዳደሩ ሃገራዊ ሃላፊነቱን በተሟላ ቁመና እንዲወጣ ለማድረግ እና እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት በትኩረት እንደሚሰሩ ማብራራታቸውን ከሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Agrégateur de contenus


የቅርብ ዜናዎች