ተቋማቱ 17ኛውን ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በጋራ አከበሩ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ፣ ሰላም ሚኒስቴር፣ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትና የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ተቋማት አመራር እና ሠራተኞች 17ኛውን ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!” በሚል መሪ ቃል በደማቅ ሁኔታ አከበሩ፡፡

በሰንደቅ ዓላማ መርሃግብሩ ላይ ክቡር አቶ ብናልፍ አንዷለም የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ፣ ክብርት ወ/ሮ አስቴር ዳዊት የኢመደአ ም/ዋና ዳይሬክተር ፣ ክቡር አቶ ሙሉቀን አማረ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ፣ አቶ ከበደ ቶሎሳ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ተወካይ ፣ አቶ ዮዳሔ አርአያሥላሴ የኢመደአ ም/ዋና ዳይሬክተር፣ አቶ ሃኒባል ለማ የኢመደአ ም/ዋና ዳይሬክተር ተወካይ ተገኝተዋል፡፡

በእለቱ የተገኙት የኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዷለም ለአራቱም ተቋማት አመራርና ሠራተኞች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ባስተላለፉበት ወቅት እንደተናገሩት ሰንደቅ ዓላማችን የኅብረብሔራዊ አንድነታችን ፣እኩልነታችን ዋስትና ነው! ሰንደቅ ዓላማችን የትናንትና ተጋድሏችን እና መስዋዕትነታችን ከዛሬ ሉዓላዊነታችን፤ የዛሬ ሉዓላዊነታችን ደግሞ ከነገ ተስፋችን እና ህልማችን ጋር የሚያገናኝ ድልድይ ነው ብለዋል፡፡ ክቡር ሚኒስትሩ አያይዘውም የነገ ህልማችን ደግሞ ሰብአዊና አኮኖሚያዊ ብልጽግናችንን ማረጋገጥ እና ተጽእኖ ፈጣሪ አፍሪካዊት ሃገር መገንባት እንደሆነ አስገንዝበው፤ የዛሬው የሰንደቅ ዓላማ ቀንን ስናከብር ለህልማችን መሳካት በጋራ ቃላችንን የምናድስበት ቀን መሆን እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በመጨረሻም በሰንደቅ ዓላማ አከባበሩ ላይ የአራቱም ተቋማት አመራርና ሠራተኞች የተጀመረውን ሃገራዊ የለውጥ ጉዞ ለማስቀጠል ቃለ ማሃላ ፈጽመዋል፡፡

Agrégateur de contenus


የቅርብ ዜናዎች