“መከላከያ ኃይላችን ግዳጁን ከሚወጣባቸው ነባር ምህዳሮች ባሻገር አዲስ የጦርነት ምህዳር በሆነው የሳይበር ምህዳር ላይም አቅም ለመገንባት እየሠራ ነው” ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሀመድ፣ የመከላከያ ሚንስትር

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

“መከላከያ ኃይላችን ግዳጁን ከሚወጣባቸው ነባር ምህዳሮች (የየብስ፣ የውሃ እና የአየር ምህዳሮች) ባሻገር የዘመናችን አዲስ የጦርነት ምህዳር በሆነው “የሳይበር ምህዳር” ላይ የሀገራችንን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ የሚያስችል አቅም ለመገንባት እየሰራ ነው” ሲሉ የመከላከያ ሚንስትር ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ገለጹ፡፡

የሀገር መከላከያ ሠራዊታችን የሀገራችንን ህገ መንግስትና ህገ መንግስታዊ ሥርዓት ከማንኛውም ጥቃት የሚከላከል እና ሉዓላዊነታችንን የሚያስከብር ጀግና ሠራዊት ከመሆኑም ባሻገር አለም አቀፍ ግዳጆችን በቁርጠኝነትና በሃላፊነት የመወጣት አኩሪ ገድል ያለው ሰራዊት እንደሆነ ጠላትም ወዳጅም የሚመሰክረው ሃቅ ነው፡፡

በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አማካኝነት ለሦስት ወራት ያህል የሳይበር ደህንነት የአቅም ግንባታ ስልጠና ሲሰለጥኑ የቆዩ የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት አባላት በዛሬው ዕለት በተመረቁበት ወቅት ተገኝተው የስራ መመሪያና ማጠቃለያ የሰጡት ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሀመድ መከላከያ ሰራዊት ከነባሩ ምህዳር ባሻገር በአዲሱ የሳይበር ምህዳር ላይም ተወዳዳሪ አቅም እየገነባ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዚህም ከነባሮቹ የየብስ፣ የውሃ እና የአየር ምህዳሮች ባሻገር የዘመናችን አዲስ የጦርነት ምህዳር የሆነው የሳይበር ምህዳርን አስፈላጊነት በውል በመገንዘብ የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ የሚያስችል የአቅም ግንባታ ሥራ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ሚንስትሯ፤ “በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አማካኝነት የተሰጠውን የሳይበር አቅም ግንባታ ስልጠና ስትከታተሉ ቆይታችሁ በዛሬው እለት የተመረቃችሁ የሰራዊታችን አባላትም ይህንኑ የሰራዊቱን ሁለንተናዊ የሳይበር ደህንነት አቅም የማሳደግ ጥረት አካል ናችሁ” ብለዋል፡፡

የመከላከያ መሠረተ ልማት ከቁልፍ መሠረተ ልማቶች መካከል የሚመደብ እንደመሆኑ መጠን በተቋሙ ላይ የሚደርስ የሳይበር ጥቃት ተፅዕኖ ዘርፍ ተሻጋሪና በሀገር ጥቅም ላይ ትልቅ እንድምታ ያለው መሆኑን ያመላከቱት ሚንስትሯ፤ የመከላከያን የኢንፎርሜሽን መሠረተ ልማት ቀን ተሌት በ24/7 ያልተቋረጠ ጥበቃ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በመጨረሻም “ከስልጠናው ባገኛችሁት ዕውቀት፣ ክህሎት እና ልምድ መሠረት ወደ ግዳጅ ስትመለሱ የዩኒቶቻችሁን አቅም ከማጠናከር ባሻገር በተቋማችሁ ውስጥ የሳይበር ደህንነት የክትትልና ሞኒተሪንግ ሥራን አጠናክራችሁ መተግበር ይጠበቅባችኋል፤ እንደምትተገብሩ እምነቴ የጸና ነው” በማለት የሥራ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

Publicador de continguts


የቅርብ ዜናዎች