“የቁልፍ መሰረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት በኢትዮጵያ” በሚል ርእስ ጥናታዊ ጽሁፍ ቀረበ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ጥቅምት 1/2017 ዓም በይፋ በተከፈተዉ የ5ኛዉ የሳይበር ደህንነት ወር ላይ “የቁልፍ መሰረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት በኢትዮጵያ” በሚል ርእስ ትኩረቱን በቁልፍ መሰረትተ-ልማቶች ደህንነት ላይ ያደረግ ጥናት ቀረብ። ጥናቱን ያቀረቡት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር የክቡር አቶ ዳንኤል ጉታ ናቸዉ።

በጥናቱ ቁልፍ መሰረተ ልማቶችን ለመለየት የሚያስችሉ አራት መሰረታዊ መስፈርቶች የቀረቡት አቶ ዳንኤል ቁል መሰረተ ልማቶች ለሀገር ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ዕድገት የማይተካ ሚና እንዲሁም፣ ከአንድ ዘርፍ በላይ የሚያገለግሉ (Interdependent) ፣ ለሀገር ግንባታ ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱና ከፍተኛ መዋለ ነዋይ የሚጠይቁ መሆናቸዉን በጽሁፉ ቀርቧል። እነዚህ ተቋማት ላይ ጉዳት ቢደርስ በብሄራዊ ጥቅምና ደህንነት፣ እንዲሁም በዜጎች ሕይወት ላይ ከፍተኛ ቀውስ እንደሚፈጥሩ ተገልጸዋል፡፡

የበርካታ ሀገራትን ተሞክሮችን ያነሱት አቶ ዳንኤል ጉታ እነዚህን ተሞክሮዎች እንደ ሀገር በመቀመር ጠንካራ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነትን ማስጠበቅ የሚያስችል ሁሉን አቀፍ አካሄዶችን መከተል እንደሚገባ ያነሱት አቶ ዳንኤል በሀገራችን አሁን እየታየ ካለው ከፍተኛ የሳይበር ጥቃት/ስጋት አንፃር፣ ወቅቱን ታሳቢ ያደረገ ስራ መስራት ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

በሀገራችን የጥቃት መጠን የደረሰበት ደረጃ እና አስጊነቱ በጥናቱ የቀረብ ሲሆን በህግ ሊሸፈኑ የሚችሉ ጉዳዮችን ለይቶ ሽፋን የሚሰጥና የተሻለ የቁጥጥር የቅድመ መከላከል፣ ፈጣን የአደጋ ምላሽ፣ የመረጃ ልውጥና የትብብርና ቅንጅት ስራዎች ዝርዝር ሁኔታ የያዘ የአሰራር ስርዓቶችን መዘርጋትና ወደመሬት ማውረድ እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል፡፡

アセットパブリッシャー


የቅርብ ዜናዎች