ሀገራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ የውይይት መድረክ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

5ተኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር የሁለተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ትኩረቱን በሀገራችን የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ ላይ በማድረግ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

የውውይት መድረኩን የከፈቱት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ እንደገለጹት እንደ ሀገር በ2004 የወጣ የኢንፎርሜሽን ደህንነት ፖሊሲ ሥራ ላይ የዋለ ቢሆንም ፖሊሲው ሙሉ በሙሉ ሥራ ላይ ውሎ በመስኩ ያሉብንን ችግሮች ፈቷል ለማለት አያስችልም፡፡

ከዚህ አኳያ በሳይበር ምህዳር ተለዋዋጭነትና ውስብስብ ባህሪ ምክንያት ጊዜውን የዋጀ እና ለተግባራዊ እርምጃ መደላድል የሚፈጥር፣ የፖሊሲ ማዕቀፍ ማዘጋጀት በማስፈለጉ የተሻሻለው ሀገራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ በቅርቡ ፀድቆ ሥራ ላይ ውሏል ብለዋል፡፡

በመሆኑም የውይይት መድረኩ ዋና ዓላማ የሀገራችንን የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ ወደመሬት ለማውረድ የሁሉም ተቋማት እና ዜጎች ሚናና ድርሻ ወሳኝ መሆኑን ለማስገንዘብና መደላድል ለመፍጠር እንደሆነ ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ተናግረዋል፡፡

Tartalom megjelenítő


የቅርብ ዜናዎች