ኢመደአ እና የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የጋራ ትብብራቸውን የበለጠ ለማጠናከር የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) እና የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በጋራ ለመስራትና ትብብራቸውን የበለጠ ለማጠናከር የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ፡፡ ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት በጋራ ሀገራዊና ተቋማዊ ጉዳዮች ላይ በአጋርነትና በትብብር ለመስራት ያስችላል ተብሏል፡፡

በመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ፊርማ ሥነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ እንደገለጹት፤ ኢመደአ እና የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከዚህ ቀደምም በጋራ ጉዳዮች ላይ በትብብር ሲሰሩ መቆየታቸውን ጠቁመው “በዛሬው ዕለት ደግሞ ትብብራችን መግባቢያ ሰነድ ወደመፈራረም ደረጃ ከፍ ብሏል” ብለዋል፡፡ ስምምነቱ የቴክኖሎጂ ልማትና ትግበራ አቅምን በጋራ ለመጠቀም፣ በሳይበር ደህንነት አቅም ግንባታ፣ በተቋማዊ ባህል ግንባታና በመረጃ ልውውጥ በአጋርነትና በትብብር ለመስራት እና ሁለቱ ተቋማት ከዚህ ቀደም ሲያደርጉት የነበረውን የትብብር ሥራ ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችል መሆኑንም ዋና ዳይሬክተሯ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በከፍተኛ ደረጃ የቴክኖሎጂ አቅሙን እየገነባ የሚገኝ መሆኑን በእለቱ በተደረገው ጉብኝት መገንዘባቸውን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሯ፤ ከዚህ አኳያ ኢመደአ የፌዴራል ፖሊስ የሚያካሂደውን ግዙፍ የቴክኖሎጂ ሽግግር የአሠራር ሥርዓቱን በማዘመንና በሳይበር ደህንነት ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት ከጎኑ ሆኖ ለማገዝ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በበኩላቸው፤ ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ውስጥ በጋራ ጉዳዮች ላይ አብሮ የመስራት ትልቅ ችግር የነበረ መሆኑን ጠቁመው “ከለውጡ በኋላ ግን ይህ በከፍተኛ ደረጃ ተሸሽሏል፣ እኛ እያደረግነው ያለነው ትብብርም ለዚህ ጥሩ ማሳየ ነው” ብለዋል፡፡ ከዚህ አኳያ በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ እና በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር መካከል እየተደረገ ያለው አብሮ የመስራት ባህልና የጋራ የመግባቢያ ሰነድ ወደመፈረም የተሸጋገረ ትብብር የሀገር ሰላምና ደህንነትን በጋራ ለማስጠበቅና ሁለንተናዊ ልማትን ለማረጋገጥ ትልቅ አስተዋፅኦ ያለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ስምምነቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረና አስጊ እየሆነ የመጣውን የሳይበር ወንጀል ለመከላከልና ወንጀሉ ተፈጽሞ ሲገኝም በአግባቡ ለመመርመርና ለፍትህ ለመቅረብ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እገዛ የሚገኝበትና ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑንም ኮሚሽነር ጀነራሉ ገልጸዋል፡፡

Sisältöjulkaisija


የቅርብ ዜናዎች