ኢመደአ እና ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በሳይበር ደህንነትና ተያያዥ መስኮች ላይ ዘላቂ ትብብር ለመፍጠር የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) እና ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በሳይበር ደህንነት፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና ተያያዥ መስኮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

በመግባቢያ ስምምነቱ ላይ የተገኙት የኢመደአ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ጉታ እንደገለጹት በሀገራችን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ትልቅ ሚናን እንደሚጫወት ጠቁመው፤ ከዚህ አኳያ የኮሚሽኑን ተልዕኮ ለማሳካት በጋራና በትብብር ለመስራት ኢመደአ ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የመግባቢያ ስምምነቱ ዋና ዓላማም ብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽንን ተቋማዊ የሳይበር ደህንነት ቁመና ለማጎልበት የሚያስችሉ የሳይበር ደህንነት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች እንዲሁም ቴክኒካልና የቴክኖሎጂ ድጋፎችን ለመስጠት የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የኮሚሽኑን የሳይበር ደህንነት ስጋት ተጋላጭነት ፍተሻና ግምገማ ለማካሄድ ብሎም ኮሚሽን የራሱን የሆነ ጠንካራ ተቋማዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲና የአሠራር ሥርዓት ለመዘርጋትና ለመተግበር ስምምነት ላይ መደረሱን አቶ ዳንኤል ጉታ ገልጸዋል፡፡

የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ተመስገን ጥላሁን በበኩላቸው እንደገለጹት፤ ስምምነቱ በሳይበር ደህንነትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከኢመደአ ቲክኒካልና የቴክኖሎጂ ድጋፎችን ለማግኘት እንዲሁም የኮሚሽኑን የመረጃ ሃብትና የኢንፎርሜሽን ሥርዓት ከሳይበር ጥቃት ለመጠበቅ የሚያስችል የቁጥጥር ሥርዓት ለመዘርጋትና ለመተግበር እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡

ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በሚይዛቸው ቁልፍ የመረጃ ሃብቶች ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነት ስጋቶችን ለመከላከልና ከተከሰቱም ሪፖርት ለማድረግና መረጃዎችን በማጋራት አስፈላጊው ምላሽ የሚሰጥበትን ሁኔታ ለመፍጠር ስምምነቱ ጉልህ ሚናን እንደሚጫወት ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን ገልጸዋል፡፡

ناشر الأصول


የቅርብ ዜናዎች